የመንከባከብ ባህል – እንጂ የጦርነት ባህል አይጠቅምም!
ኖቬምበር 17-25፣ 2023
በወታደራዊነት አገዛዝ/ ሚሊተሪዝም/ ላይ ዓለም አቀፍ የድርጊት ቀናት
በተመሳሳይ ጊዜ ከሚካሄዱት ከዓለም አቀፋዊ የፀረ-ወታደራዊ አገዛዝ/ ሚሊተሪዝም/ እርምጃዎች ጋር በተለያዩ የሀገር አውዶች የተደራጁ፣ በአለም አቀፍ ደረጃ ወታደራዊ አወቃቀሮችን እና ከበዝባዥ እና አድሎአዊ ስርዓቶች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመቃወም ሰፊ ተቃውሞ ይዘጋጃል።
የወታደራዊነት አገዛዝ/ ሚሊተሪዝም/ በስፋት መቀበል የቡርጂዚ አስተሳሰቦች እና ርዕዮተ ዓለም ላይ የተመረኮዘ ነው። በዚህ ጊዜ ይምናያቸዉን ችግሮች አንደ መደበኛ ክስተት በማየት የካፒታሊዝምን/የገበያ መር ስርአት፣ የቅኝ ግዛት ህልውናን ለማረጋገጥ አደጋዎችን እንደ “አስፈላጊ ክፋት” ይታያሉ፡፡
እነዚህ ስርዓቶች በሰው ልጅ ህይወት ላይ ቀጣይነት ባለው ውድመት ላይ የተመሰረቱ ናቸው ሰራተኛው ማህበረሰብ፣ አካል ጉዳተኞች ፣ የተገለሉ ጾታ አባላት ፣ ጥቁር ፣ እና የቦታው ተወላጅ ሰዎች – እንዲሁም በአጠቃላይ ሕይወትን ፣ ተፈጥሮን ፣ ፕላኔትን የሚያፈናቅልና አደጋ ላይየ የሚጥል ርዕዮተ ዓለም ላይ የተመሰረተ ነዉ።
ከዚህ በላይ የወታደራዊነት አገዛዝ/ ሚሊተሪዝም/ በነጭ የበላይነት ፣ በካፒታሊዝም እና በወንዶች የበላይነት ስም ፉክክር እና የጦርነት አስተሳሰብን ያጠቃልላል። ፣ ገዳይ ድንበሮችን ማቋቋም እና ቀጣይነት ያለው የጥቁር ፣ እና የቦታዉ ተወላጆች ሰብአዊነት ማጉደል እና ግድያ ያስፋፋል ።
ስለዚህ ሕይወትን የሚያሻሽሉ ትቅዋማትን እና የአኗኗር ዘይቤዎችን ከፈለግን እኛ እራሳችን መፍጠር አለብን። የፕላኔቷ ወታደራዊ አገዛዝ ጨቋኝ ስርዓቶችን ማቆም ማለት ጨቋኝ ስርዓቶችን ማጥፋት እና በምትኩ ለወደፊት መልካም ራዕይ ለመጀመር መሰማራት ማለት ነው
ስለዚህም ከ 17 እስከ 25 ቀን 2023 ዓ.ም ባለዉ አንድ ሳምንት ዉስጥ በተለይ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ የሆነ ፣ ዓለምአቀፋዊ ፣ የወንድ የብላይነትን የማያምኑ የተለያዩ የወታደራዊነት አገዛዝ/ ሚሊተሪዝም/ የሚቃወሙ ጥበባዊ አለያ ድርጊትዊ ፕሮግራሞችን ለማዘጋጅት ለሚፈልጉ የተለያዩ ግለሰቦችን እንዲሁም ማህበራትን እንጋብዛለን። ትናንሽ ድርጊቶችም/ ፕሮግራሞችን ጥሩ ተቀባይነት አለዉ ።ስዊዝን አስመልክቶ የጦር መሳሪያ አምራች እና አከፋፋይ እንደመሆንዋ መጠን ሂስ ሰጪ ዓለምአቀፋዊ የትግል እና የተቃዉሞ ጮራ ያስፈልጋል።
ተቃዉሞዉ በጦር መሣሪያ ኢንዱስትሪዎች እንደ Ruag /ርዋግ/፣ Thales /ታለስ እና Rheinmetall ራይን ሜታል ያሉ የጦር መሣሪያዎቻቸውን አምራች እና አከፋፋይ በዓለም ዙሪያ ወደ ውጭ በሚልኩ ለይ ነዉ።
ተቃዉሞዉ በወታደራዊ መሠረተ ልማት እና በክትትል ቴክኖሎጂዎች የተደገፉ የአውሮፓ ህብረት ድንበሮችን ወታደራዊ እና ስደተኞችን ለተጨማሪ ሞትና እንግልት የሚዳርጉ የአውሮፓ ህብረት መርሆችን ከአዉሮፕ ትነስቶ እስከ ሜዲትራኒያን ባህር እስከ ሊቢያ፣ ሞሮኮ፣ ሱዳን፣ ኒጀር እና ሌሎች ሀገራትን የሚነካ ነው።
ተቃዉሞዉ በሰዎች ላይ የሚደረገዉ ቁጥጥር እና ጥቃትን ህጋዊ መልክ እነዲኖረዉ የሚያደርጉትን ክፍሎች ምንም እንኾን ህጎቹ ዘረኛ የደህንነት ትረካ ላይ የተመረኮዘ ስለሆነ።
ፍላጎታችን እና ጥረታችን የአለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪ እንዲጠፋ በምትኩ የጋራ እና የእንክብካቤ መዋቅሮችን የሚያስተዋወቅ ባህል እንዲስፋፋ ነዉ.
ፍላጎታችን እና ጥረታችን ሕይወትን መደገፍ ለሚያስችል አካባቢ፣ ሕይወትን መደገፍ ለሚያስችል መሬት እና ወደፊት ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ነዉ።
ለሁሉም ሰው ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ነፃነት።
አጋርነታችን በአለም ለይ ለሚኖሩ ለተጨቆኑ፣ ለተበዘበዙት እና ለተነጠቁት ወገኖች በሙሉ።
ከቅኝ ግዛት ነጻ የሆነ ፣ ከጾታዊ የበላይንት ነጻ የሆነ አለማቀፋዊ አብዮታዊ ሂደት!
ፕላኔቷን የወታደራዊነት አገዛዝ/ ሚሊተሪዝም/ ነፃ አድርጉ!